በሰሜን ሸዋ ተሬ ግንባር የመንግስት ሰራዊት በድሮን በታገዘ ከፍተኛ ጥቃት መፈጸሙ ተሰማ።
የፋኖ ሕዝባዊ ኃይል አለ በሚል መከላካያ በተሬ ግንባር ለዩ ሰሙ ጃብር ወክፈሌ ስርጥ በሚባል አካባቢ ቅዳሜ ነሐሴ 27 2015 በከፈተው ጥቃት በርካታ የሰራዊቱ አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው የኢቪኤን ምንጮች ገልጸዋል።
ኮረብታማውን ቦታ ለመቆጣጠር የሞከረው መከላከያ በገላጣው ሜዳ ላይ በነበረው ውጊያ ብዙ ወታደሮች እንደተጎዱበትና በግንባሩ የተሰዉ ወታደሮች ወደ ሸዋሮቢት ሲጋዙ እንደነበር የዓይን እማኞች ገልጸዋል።
በግንባሩ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የተነገረው ሰራዊት የድሮን እገዛ የተላከለት ሲሆን በሰላማዊ ዜጎች ላይ ሳይቀር ጭፍጨፋ አንዳደረገ ለመረዳት ተችሏል።
መከላከያ ኮረብታውን ለመቆጣጠር ባመራበት ወቅት የግብርና ባለሞያዎችን ሳይቀር የወታደር ልብስ አልብሶ አቅጣጫ አንዲመሩ በማድረግ አንደነበር የአካባቢው ቅዳሜ ገበያተኛ መመልከቱ ተገልጿል።
ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል የተባለው ሰራዊት ምሽቱን ወደኋላ ተመልሶ ሸዋሮቢት ከተማ ማደሩም ታውቋል።
በዚህ ክፉኛ የተበሳጩት የጦሩ አመራሮች የሸዋሮቢት የመንግስት ሹመኞችን እያሰሩ አንደሆነ ተጠቁሟል።የከተማው ከንቲባ አቶ ተስፋዬ መንግስቱ፣አስተዳዳሪው ሽመልስት ችሮታው፣አፈጉባኤው አቡሽ አበበ፣ የትምህርት ኃላፊው ሽመልስ ሀሰንና የሸዋ ሮቢት የገጠርና የክተማ የጸጥታና ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር መሆናቸውን የኢቪኤን ምንጮች ገልጸዋል።
ከካቢኔዎቹ በተጨማሪ የአክባቢው ነዋሪ በገፍ አየታሰረ ህወሓት ባሰገነባው የሸዋሮቢት አስርቤት እየተጋዙ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።ከዚያም አልፎ ከህወሓት ጋር በነበረው የሰሜኑ ጦርነት ወዶ ዘማቾች ተመዝግበውበት የነበረው ዶሴ እየተበረበረ የፋኖ ታጋይ ለመሆን የወጣውን አማራ ለመለየትና ለማደን እየተጠቀሙበት መሆኑ ተመልክቷል።በዚህ መሰረት በቤቱ የተገኘ የቀድሞ ዘማች ጠቁም እየተባለ ድብደባ እየተፈጸመበት ወደ አስርቤት ይወሰዳል ተብሏል።
በታያያዘ ዜና ከሸዋሮቢት አጣዬን አለፍ ብሎ በምትገኘው ማጀቴ ከባድ ውጊያ አየተካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።