በትግራይ 90 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ኑሮውን የሚገፋው በሰብአዊ የምግብ አርዳታ እንደሆነ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።
አቶ ጌታቸው ከተባበሩት መንግስታት ድረጀት ተውካዮች ጋር በመቀሌ ተገናኝተው ባደረጉት ንግግር 90 ፐረሰንቱ ሕዝብ በእርዳታ ላይ የተመረኮዘ ሕይውት ስለሚገፋ የተባበሩት መንግስታት ወኪል ድርጅት የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት USAID በአስቸኳይ የእርዳታ እጃቸውን አንዲዘረጉ ተማጽነዋል።
ትግራይ ከእነዚህ ድርጅቶች ብቻ ሳይሆን ከመላው ዓለም አፋጣኝ አርዳታ እንደሚያሻት ተገልጿል።በጦርነት በተፈጠረው ውድመት የተነሳ የትግራይ ሕዝብ ለማያባራ መከራ መዳረጉን የተናገሩት አቶ ጌታቸው ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ቢሞከርም ትህምህርትቤቶቹ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ጉዳት ስለደረሰባቸው ጥረቱን ፈታኝ አድርጎታል ብለዋል።
ሕዝቡ ከተጋለጠበት ተከታታይ መከራ ለመውጣት ሰፊና የተቀናጀ ጥረት አንደሚጠይቅ ተናግረዋል።ባለፈው መጋቢት ወር ውስጥ ለትግራይ ክልል ለእርዳታ በቀረበ አህል ላይ መጠነ ሰፊ ዘረፋ በመፈጸሙና ለገበያ ቀርቦ ሲሸጥ በመታየቱ የተባበሩት መንግስታት እርዳታውን ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ ዩኤስኤአይዲ ተመሳሳይ እርምጃ ወስዶ ቆይቷል። በወቅቱ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ለከፋ ረኃብ መጋለጡ ተጠቁሞ ነበር።
ከምግብ ዘረፋው በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ንብረት የሆነ 500 ሺ ሚሊዮን ሊትር የነዳጅ ዘይት በክልሉ አስተዳደር በመሰረቁ የእርዳታ እንቅስቃሴውን ክፉኛ አስተጓጉሎት እንደነበር አይዘነጋም።ላለፉት ስድስት ወራት የተቋረጠው የምግብ እርዳታ የክልሉን ችግር አወሳስቦታል።በዚህ ምክንያት የጤና ቀውስ እየተባባሰ ነው። እነዚህ ችግሮችና አሁን የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ወረራ የትግራይ ሕዝብ ላይ ዳግም የረኃብ ዘመን አንዳይመጣ ተሰግቷል።
በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ ከፍተኛ የሚባሉ ወንጀሎች መበራከት ሕብረተሰቡን ለስጋት ከመዳረግ ባላፈ የኑሮው ፈታኝ ነት ሕዝቡ ባለው አስተዳደር ላይ ተቃውሞውን እያሰማ እንደሆነ የሀገር ውስጥ የመገናኛ አውታሮች እየዘገቡ ነው።