08-30-2023

በደብርታቦር ከተማ በመከላካያና በፋኖ ሕዝባዊ ታጋዮች መካከል በነበረው ጦርነት ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ተገድለው መገኝታቸውን የኢቪኤን ምንጮ ገለጹ።

 
ትላንት ኢቪኤን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ከነሐሴ 20 እስከ ነሐሴ 22 ለሦስት ቀናት በዘለቀው ውጊያ ከ5 ሰዎች በላይ መገደላቸውን የጠቆሙ ሲሆን ዛሬ ደግሞ አንድ በሰፌድ ስፌት ስራ የሚተዳደሩ አድሜያቸው በ50ዎቹ ውስጥ የሚገኙ መነኩሴና አንድ የፋኖ ታጋይ ተገድልው መገኛታቸውን አስርድተዋል።
 
በሌላ በኩል የደብረታቦር ሆስፒታል በከባድ መሳሪያ መመታቱንና 5 ታማሚዎች እንዲሁም ሌሎች  20 ሰዎች ላይ ጉዳት መድርሱን ቢቢሲ የዘገበ ሲሆን ኢቪኤን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች የከባድ መሳሪያ ፍንጣሪ ሆስፒታሉ አካባቢ ያሉ ሰዎችን ማቁሰሉን ሲያረጋግጡ ሆስፒታሉ ላይ ጉዳት ደርሶ እንዳላዩ ጠቁመዋል።
 
ጦርነቱ ከቆመበት ከነሐሴ 22  ጀምሮ ከተማዋ ጸጥ ረጭ ብላ የምትገኝ ሲሆን ከጋሳይ መስመር ከሚመጡ ጥቂት መኪኖች በስተቀር ምንም ዓይነት የትራንስፖርት አንቅስቃሴ የለም ተብሏል።በከተማዋ ቋሚ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት ባጃጆች አስካሁን የአንቅስቃሴ እገዳ እንደተጣለባቸው ነው።
 
ሕብረተሰቡም ከቀኑ 12 ሰዓት በኋላ የሰዓት እላፊ እንደተጣለበት ቆይቷል። መከላከያ በተቆጣጠራት ደብረታቦር ከተማ ፋኖ ጠቁሙ በሚል ወከባና ማስፈራራት አየተፈጸመ መሆኑም ተገልጿል።