08-30-2023
ታዋቂው ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ ነሐሴ 19 2105 የለቀቀው እንደ አባቴ እወድሻለሁ የተሰኘው አዲሱ አልበሙ የሲዲ ሽያጭ ገበያ ላይ እንዳይውል መደረጉን ገለጸ።
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች አያዞሩ የሚሸጡ ነጋዴዎች በፖሊስ ክለከላ አንደተፈጸመባቸው አቡሽ ተናግሯል።
የክልከላው ምክንያት ባይታወቅም ሀግራዊ አንድነትን የሚደግፈው አቡሽ ክ8 ወራት በፊት የለቀቀው “አውጡት ከፓርላማው” የሚለው ዘፈኑ በገዢው ስርዓት እንዳልተወደደለት ሲነገር ቆይቷል።አቡሽ በዘፈኑ ሕገመንግሱቱን ጠቅሶ በውስጡ ያለው አንቀጽ እንዲወገድ ይጠይቃል።
“ጸጋውን ሳይነሳን በችግር ጎበጥን፤
በእናንተው እንቶ ፈንቶ ነፍስ እየገበርን።
የካቻምናው እንቅፋት ዘንድሮም ከመታን፤
የታለ እውቅታችሁ ያለንን ካሳጣን።
አውጡት ካፓርላማው ያንን የሞት መዝገብ
የጨው ዘር አንዳንሆን አንድንሰባሰብ።
ለሰው ቦታ የለው ዜጋ አያውቅ ዘውግ አንጂ
ስንት ዓመት አየነው ለማንም አይበጅ።
አትማሉ በሱ አጃችሁን ጭናችሁ
በየአንጓው ከፋፍሎ መድገም ካላሻችሁ”
አያለ በግጥሙ ይማጸናል፣ይወትውታል።
ይኽ ነጠላ ዜማው በአዲሱ አልበም ተካቶ አንደሚገኝ ከግል የማህበራዊ ገጹ ለመረዳት ተቸሏል።
አቡሽ በምርጥ የቦረና ባህላዊ ዘፈኖቹ የሚታወቅና የሚወደድ ሲሆን በለውጡ ሰሞን “አነቃቃን” የሚል የድጋፍ ሙዚቃ ማስደመጡ ይታወሳል።