የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ቢሮ ከሐምሌ ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት የአማራ ታጣቂ ፋኖዎችን ለመበተን ባደረገው ሙከራ በተነሳ ግጭት ቢያንስ 183 ሰዎች መገደላቸውን ገለፀ።
ቢሮው በዛሬው ዕለት በኢትዮጲያ የሰብአዊ መብት አያያዝ እየከፋ እንደሄደና ከ1000 በላይ ሰዎች ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላ መታሰራቸውን አስታውቋል። “ለእስር የተዳረጉት አብዛኞቹ የአማራ ብሄር ተወለጆች የፋኖ ደጋፊዎች ናችሁ” በሚል እንደሆነ አመልክቷል።
ያለማጣራት በማን አለብኝነት የሚፈጸመው የጅምላ እስር ማጐሪያ ካምኘ ለእስረኛ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ባለሟላ መልኩ ነው ሲል የተግበሩት መንግስታት ገልጿል።
ቢሮው በተጨማሪ በአንድ ክስተት ብቻ ፍኖተሰላም ከተማ ላይ በተደረገ የአየር ጥቃት 26 ንፁሐን ተጋድለው መንግስት አስተያየት ሳይሰጥ ቀርቷል።
የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ጋር በነበረው ጦርነት የአማራ ፋኖዎች ለሁለት ዓመታት ያህል ከመንግስት ጐን መሰላፈቸውና የህይወት መስዋዕትነት መክፈላቸው ይታወሳል::
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገሪቷ በተደጋጋሚ የሚነሱ የብሄር ግጭቶችን መቆጣጠር እንደተሳናቸውና ሀገሪቷ ለከፋ እልቂት እየተዳረገች መሆኗን የውጭ ሀገር ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።