ክልሎቹ ለዘንድሮው የምርት ዘመን 20 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም በውጭ ምንዛሪ እጥረትና በአቅም ውስንነት 13.6 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ ከውጭ መገዛቱ ተገለጸ። የግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ክልሎቹ የተለያዩ ፍላጎቶች ቢኖራቸውም በአገራዊ የአቅም ማነስ ምክንያት በቂ ድጋፍ እያገኙ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ለ13 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ግዢ አንድ ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገ ሲሆን፥ ይህም ባለፈው አመት በ650 ሚሊየን ዶላር ከተገዛው ጋር ተቀራራቢ ነው ብለዋል። ተጨማሪ ማዳበሪያ እንደሚያስፈልግ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ አገራችን ገበሬዎች የሚያስፈልጋቸውን ያህል ማደበሪያ ለማቅረብ የሚያስችል አቅም የላት ም ብለዋል። የአመቱ የመጀመሪያ እቅድ 12 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል ለመግዛት ቢሆንም ተጨማሪ 800,000 ኩንታል ለትግራይ ክልል በመመደብ የአመቱን አጠቃላይ ግዥ ወደ 13 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ሊያሳድገው እንደቻለ ጠቅሰዋል።
ሚኒስትሩ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከ15 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ተጠቅማ አታውቅም። በዚህም መሰረት ባለፈው አመት የተገዛውን 13 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ጨምሮ በአጠቃላይ 15 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ አርሶ አደሮች ያገኛሉ። በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች የማዳበሪያ እጥረት አርሶ አደሮች ስጋታቸውንና ተቃውሞ ሲገልጹ ቆይተዋል።
ለ50 ኪሎ ማዳበሪያ ከ3,000-4,000 ብር ይከፍሉ የነበሩ አርሶ አደሮች አሁን በጥቁር ገበያ ከ10,000 ብር በላይ እየከፈሉ ነው። የሚኒስትሩ ማብራሪያም ሆነ የገበያ ባህሪ በማዳበሪያ አቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን ልዩነት ያመለክታሉ። ዘንድሮ በጥቅምት ወር የማዳበሪያ ግዥ ውል ቢፈራረምም፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ እና በአሰራር መዘግየት ሳቢያ ግብይቱ ዘግይቷል። በተገኘው መረጃ መሰረት አብዛኛው የተገዛው ማዳበሪያ (87 በመቶ) ጅቡቲ ደርስዋል።
በጅቡቲ ከገባው አጠቃላይ ማደበሪያ ውስጥ (11.9 ሚሊዮን ኩንታል) አብዛኛው (10.7 ሚሊዮን) ከውጭ የገባ ነው። ወደ ጅቡቲ ከገባው ማዳበሪያ 68 በመቶው ብቻ ለገበሬው ደርሷል።