በሰሜን ሸዋ በምትገኘው ማጀቴ 31 ሰላማዊ ዜጎች በመከላከያ ሰራዊት መገደላቸው ተገለጸ።

በማጀቴ በመከላከያና ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ መካከል ሲካሄድ የነበረው ውጊያ ፋኖዎች የውጊያ አቅጣጫ ቀይረው ከወጡ በኋላ አንጻራዊ ጸጥታ ሲገኝ መከላከያው በነዋሪው ላይ የሚዘገንን አርምጃ እየወሰደ እንደሆነ የኢቪኤን ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል።
በርካታ ውታደሮች የተጎዱበት መከላከያ ግብታዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኢቪኤን  ያነጋገራቸው አንድ ቤተሰባቸውን ያጡ ነዋሪ አራጋግጠዋል። በተወሰደ የበቀል ኃይል እርምጃ 31 ሰላማዊ ዜጎች ሕይወታቸውን ተነጥቀዋል።
“ዛሬ ሰኞ ውገኖቻችንን ልንቀብር ስንወጣ አስከሬን አንኳ እንዳናነሳ ከልክለውናል”ያሉት የቤተሰብ አባል “ኃዘናችንን እንዳንወጣ ማድረግ ብቻ ሳይሆን አስከሬን አስቀምጠን ስብሰባ እንድንሰበሰብ አስገድደው ኃዘናችንን መሪር አድርገውብናል” ብለዋል።
የመከላካያ አዛዥ ባዘዙት መሰረት የማጀቴ ነዋሪ ስብሰባ እንዲሰበሰብ ቤት ለቤት አያስገደዱት መሆኑ ለመረዳት ተችሏል።
ከወር በላይ ከፍተኛ ጦርነት ከነበረባት እንሳሮ በቅርብ ርቀት በምተገኘው እነዋሪ የገባው ላላፉት ሁለት ቀናት መከላካያ ፋኖዎችን ጠቁሙ በሚል እንግልትና ድብደባ መፈጸም መጀምሩንና አብዛኛው ወንድ ወደ ጫካ መግባቱን የአካባቢው ነውሪዎች ለኢቪኤን ገልጸዋል።
ላሊበላ ከተማ መሉ ለሙሉ በመከላከያ ቁጥጥር ስር ያለች ሲሆን እለታዊ የአውሮፕላን በረራ እየተካሄደ ሲሆን የንግድና የቱሪስት እንቅስቃሴ ግን እንደሌለ የከተማው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ነገርግን መከላካያው ከላሊበላ ከተማ ወጣ ብለው በፋኖ ቁጥጥር ስር ወዳሉ ስፍራዎች እንደማይንቀሳቀሱ ጠቁመዋል።